Jul 27 / ብሩክቲ

ባህሪን መቅረጽ፡ ግልፍተኛ ባህሪን የያዙ ልጆችን የመቅረጽ ጉዞ!

ባህሪን መቅረጽ፡ ግልፍተኛ ባህሪን የያዙ ልጆችን የመቅረጽ ጉዞ!


መቅረጽ በህይወታችን በሙሉ በባህሪ ላይ ሊተገበር የሚችል ጽንሰ-ሀሳብ ነው። እኛ ወላጆች እና አሳዳጊዎች የልጆቻችንን ባህሪ በመቅረጽ ረገድ ትልቅ ድርሻ አለን። ባህሪያት በብዙ ምክንያቶች ተጽዕኖ እንደሚኖራቸው ይታወቃል። እንደ ወላጅ እና አሳዳጊ፣ ልጆቻችን ከተወለዱ ጀምሮ ባህሪያቸውን እንቀረፃለን። የሚኖራቸው ባህሪም በተቀረጹበት መንገድ ይሆናል። ይህም ከንግግራቸው ጀምሮ እስከ ማልቀስ እና ነገሮችን የሚይዙበት ሁኔታ፣ ከሌሎች ጋር ያላቸው መስተጋብር፣ አዎንታዊ የሐሳብ ልውውጥ የሚያደርጉበት መንገድ እና ጥሩ ማህበራዊ እና ስሜታዊ ችሎታዎችን ያሚያዳብሩበት መንገድን ይወስነዋል። እነዚህ ሁሉ የልጆችን ባህሪ በምንቀርፅበት መንገድ ላይ የተመሰረቱ ናቸው።
ወደ ልጆቻችን "ግልፍተኛ" ባህሪ ስንመጣ, አታበሳጩዋቸው። ይህን አላስፈላጊ የሆነ የልጆችን ባህሪ መግራት እንችላለን። ልጆቻችን እያደጉ ሲሄዱ፣ በባህሪያቸው ዙሪያ የተለያዩ ፈተናዎችን የምንጋፈጥ ሲሆን ምንአልባትም ራሳችንን የምንይዝበት፣ የምንበሳጭበት፣ እንዲሁም አንድ አንድ ጊዜም የልጆችን “መጥፎ” ባህሪይ ለመቅረጽ በሞከራናቸው እና በወደቅንባቸው ብዙ ሙከራዎች ተስፋ የምንቆርጥበት ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል። ይህ የልጆች ባህሪ ከእምቢተኝነት እስከ ትምህርት ቤት ውስጥ ጥሩ ባህሪን እስካለማሳየት፣ የመኝታ ጊዜ ላይም ካለመተኛት እስከ ግልፍተኛ ባህሪ እና ሌላ የትኛውም በማይፈለግ ባህሪ የመጣ ጥሩ ያልሆነ ነገሮችን እስከማያዝ ሊደርሱ ይችላሉ።
መቅረጽ በሚባለው መሳሪያ ስላለን፣ ተስፋ አለን። ነገር ግን ቅጽበታዊ አይደለም። ላቅ ያላ ትዕግስትን፣ ብዙ ሙከራዎች እና ውድቀቶችን፣ ብዙ ውጣ ውረዶችን፣ ጽናትን እንዲሁም “ጥሩ” ብለን የሰየምናቸውን ነገሮች ማወቅን ያጠቃልላል። እነዚህ ነገሮች የልጆችን አላስፈላጊ ባህሪያትን ለመቅረጽ ወላጆች እና አሳዳጊዎች ወሳኝ ናቸው። የልጃችንን ባህሪ ለመቅረጽ አንዱ እና ዋነኛው ቁልፍ ጥንካሬዎቻቸውን እና ድክመቶቻቸውን ማወቅ ነው። እዚህ ላይ ሌላው ቁልፍ ነጥብ እንደ ወላጆች እና አሳዳጊዎች ባለን ሚና የራሳችንን ጥንካሬዎች እና ችሎታዎች ማወቅ ነው። ከልጆቻችን ጋር አንድ ሰአት ማሳለፍ እና ባህሪያቸውን ስለመቅረጽ ማውራት ከባድ ሊሆን ይችላል። እያደረግን ያለነውን ነገሮች መከለስ እና ከልጆቻችን ጋር ጥሩ ፕሮግራም ማውጣት፣ የልጆቻችንን ባህሪ በመቅረጽ እንዲሁም ጥሩ እና የተስተካከሉ ልጆች እንዲሆኑ ትልቅ ሚና ይኖረዋል። በተዘዋዋሪ የልጆቻችንን "መልካም" ባህሪ ለመቅረጽ ሁልጊዜ ያደረግነውን ነገር ለመለወጥ በመሞከር፣ የራሳችንን ባህሪያትም ጎን ለጎን እየቀረጽን መሆኑን ልብ ልንለው ይገባል። እዚህ ላይ አንድ ልናውቀው የሚገባ ነገር ቢኖር በማንኛውም የህይወታችን ዘርፍ ለውጥ ለማድረግ ቃል በገባን ቁጥር፣ በተለይ በወላጅነት ዙሪያ፣ ፍጽምና የጎደለው እንደሚሆን እና ስማችንን እንደመጥራት ቀላል እንዳልሆነ መረዳት አለብን።
እንደ ምሳሌ, "ግልፍተኛ"ን ባህሪን እንዴት መቅረጽ እንዳለብን እንይ። በቅድሚያ ልጆቻችን “ግልፍተኛ” ባህሪያቸውን የሚያነሳሳባቸው ነገሮችን ለይተን ማወቅ ይኖርብናል። "ምንጩን ማወቅ ችግሩን ለመፍታት ይረዳል!!" ነገር ግን፣ ልጆች ለአብዛኛው ነገር አዲስ ናቸው (ለስሜቶቻቸውም ጭምር)። የልጆችን ባህሪይ በመቅረጽ ውስጥ እንደ ወላጅ እና አሳዳጊ አርዓያ መሆን ያስፈልጋል። ልጆች ምን እያደረግን እንደሆነ በየጊዜው ይመለከታሉ። ሌላው መንገድ ልጆችን ለማረጋጋት እና ለማነጋገር ወጥነት ባለው ሁኔታ ቃላትን እና የእጅ ምልክቶችን መጠቀም ነው። እንዴት ምላሽ እየሰጡ እንደሆነ እንዲያውቁ ሲያደርጉ፣ ልጆች ምላሻቸው ምን አይነት ተጽዕኖ እያመጣ እንዳለ እንዲሁም ራሳቸውን ከ”ግልፍተኝነት” መቆጠብ እንዳለባቸው ይማራሉ። በተጨማሪም፣ ግልፍተኛ ባህሪን በመላበሳቸው እያመጣ ያለውን ውጤት ማስረዳት ተገቢ ነው። ይህ የልጆችን ባህሪ በሚቀረጽበት ጊዜ ትልቅ መሰረት ይሆናል። የልጆችን ባህሪ መቅረጽ እዚህ ላይ ይመጣል። እድሜያቸውን እና ልምዳቸውን በፍጥነት ማሳደግ ስለማንችል፣ ትንንሽ የሚመስሉ ማሻሻያዎቻቸውን በማወደስ እንቀርጻቸዋለን። የልጆችን ባህሪ ለመቅረጽ ጊዜ በጣም አስፈላጊ ነው። ዋናው ነገር ባህሪን በማሻሻል ጉዞ ላይ ትናንሽ ስኬቶችን ማጠናከር ተገቢ ሆኖ እናገኘዋለን።
ጥሩ ዜናው ባህሪን መቅረጽ ይቻላል። የልጆቻችንን አላስፈላጊ ባህሪያት መቅረጽ እንችላለን። ሁሉም ሂደቶችም ልምምድን፣ ጽናትን፣ ክትትልን፣ ማሻሻያዎችን እና በሂደቱ ላይ የሚመዘገቡ ትንንሽ ስኬቶችንም መቀበልን ይፈልጋል። ራሳችንን እንደ ወላጅ እና አሳዳጊ የሚያጠነክሩን ግቦች ያስፈልጉናል። ውጤቱም የድሮውን አላስፈላጊ ባህሪ በመተካት ወደ አዲሱ ባህሪ ልጆች እንዲገቡ ይረዳቸዋል። በአጭር ጊዜም ውስጥ “መጥፎ” የተባለው ወደ “ጥሩ” ይቀየራል።