የልጆች ነጻነት
ልጆች ለሁሉም ነገር አዲስ እንደመሆናቸው መጠን፣ ነፃነትን በዉስጣቸው ማዳበር በቀላሉ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሊደረግ የሚችል ሥራ አይደለም፤ ተጨማሪ ትዕግስትን የሚፈልግ ሂደት ነው። ወላጆች እና አሳዳጊዎች የዕለት ተዕለት ስራቸዉን ልጆች እንዲሰሩት ከማድረግ ይልቅ ወላጆች በራሳቸው መስራትን ይመርጣሉ፣ ምክንያቱም ትንሽ ጊዜ ስለ ሚወስድባቸው። ችኮላን ማስወገድ ልጆች ነገሮችን በራሳቸው እንዴት ማድረግ እንደሚችሉ ለማስተማር የሚረዳ ቀላሉ መንገድ ነው። ልጆቻቸው ነገሮችን በራሳቸው መምራት እንዲችሉ የማይፈቅዱ ወላጆችና አሳዳጊዎች ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ የሚያመዝን ይሆናል። ልዩ ፍላጎት ያላቸውን ልጆችን በልዩ ሁኔታ ለአዋቂነት ለማዘጋጀት ከአሁን ጀምሮ ነፃነት በዉስጣቸው መገንባት መጀመር አስፈላጊ ነው። የሚከተሉት ምክሮች ልጆች ነፃነትን እንዲማሩ ለማድረግ የሚረዱ ዘዴዎች ናቸው። አዳዲስ ስራዎችን በቅደም ተከተል የማስተማር ዘዴን መጠቀም፡- ህፃናት የልጅነት ነፃነት እንዲያገኙ፣ በየጊዜው አዳዲስ ሥራዎችን በራሳቸው ማካሄድ እንዲችሉ እድሉ ሊሰጣቸው ይገባል። ወላጆች ለልጆቻቸው በቅደም ተከተል የማስተማር ዘዴን በመጠቀም እና ቀስ በቀስ አዳዲስ ክህሎቶችን በማስተማር በሂደቱ ውስጥ ቁልፍ የሆነዉን ሚናን መጫወት ይችላሉ። ወላጆች በተለይም ደግሞ፣ ልጆቻቸውን በመንከባከብ እና በመወከል እራሳቸው ውሳኔ በመወሰን በርካታ ጊዜያትን ያሳለፉ ከሆኑ፣ መጀመሪያ ላይ ልጆቻቸውን ስለነፃነት ማስተማር ሊከብዳቸው ይችላል። ሆኖም ግን ወላጆች በወጥነት እና ተግባሩን ልጆቻቸው በራሳቸው ማድረግ እንደሚችሉ በሚጥብቁበት ጊዜ፣ ድል የመቀዳጀት አጋጣሚያቸው ሰፊ ይሆናል። ህቅምን የሚመጥኑ ተስማሚ ነገሮችን ብቻ ማመቻችት እና ማሳካት፡ ይህ ዓይነት አስቸጋሪ ሁኔታ ያለባቸው ወላጆች በልጆቻቸው ውስጥ የሃላፊነት ጫና እንዳይኖር በመፍራት ብዙውን ጊዜ ነፃነትን ለማጎልበት ፈቃደኞች አይደሉም። ይሁን እንጂ ልጆቻቸው ልክ እንደ እኩዮቻቸው ነፃነትን የማዳበር ፍላጎት እንዳላቸው ሊገነዘቡ ይገባል።
ነፃነትን ለማግኘት እንቅፋቶችን ማሸነፍ- ልጆቻቸው የመጨነቅ ወይም የመረበሽ ምልክት ሲያሳዩ ጣልቃ ለመግባት የሚታገሉ ወላጆች ክፍሉን ለቀው በመዉጣት ልጆቻቸው ወደ ነበሩበት እንዲመለሱ ወይም እርዳታ እንዲጠይቁ አጋጣሚዉን መስጠት ይኖርባቸዋል። ወላጆች ለልጆቻቸው የሚያስፈልጋቸውን እርዳታ መስጠት ያለባቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚጨምር ጭንቀት እና መረበሽ ሲሰማቸው ብቻ ነው። ልጆች አንድን ሥራ ለማጠናቀቅ የሚያደርጉት ጥረት ሳይሳካ ሲቀር ቅር እንደሚያሰኛቸው ሊገልጹ ይችላሉ፣ቢሆንም ግን ወላጆች በጥሩ ሁኔታ እየተከናወኑ ያሉ ሂደቶችን እና ሥርዓቶችን በማመስገን ላይ ማተኮር ይኖርባቸዋል።
ችሎ ማሳለፍን መማር፦ወላጆች ልጆቻቸው በማንኛውም የእድገት ደረጃ ላይ ተጨማሪ ኃላፊነትን እንዲወስዱ ለማድረግ የሚያበረታቱባቸው አጋጣሚዎች አሉ። ወላጆች ቀደም ብለው በልጆቻቸው ላይ ነፃነትን ማዳበር ሲጀምሩ፣ ልጆች በእራሳቸው ሁሉንም ነገር ለማድረግ መማር ቀላል ይሆንላቸዋል ።
ራሱን የቻለ እና በነፃነት የተሞላ ልጅ ማሳደግ መልካም የሆነ መንገድ መከተልን ይጠይቃል፡ ልጆቻችሁ እንዲያድጉ፣ እንዲመራመሩ እና እንዲማሩ የማድረግ ነፃነትን መስጠት ትፈልጉ ይሆናል። ነገር ግን ደግሞ እርዳታ በሚፈልጉበት በማንኛዉም ጊዜ እነሱን ለመደገፍ እንደምትገኙላቸው እንዲያውቁ ትፈልጋላችሁ። ትክክለኛውን ሚዛን ለማግኘት አንዳንድ ሙከራዎች እና ስህተቶች ይኖሩታል፣ ስለሆነም በመጨረሻ የሚገኘው ሚዛናዊ የሆነዉ ነገር ከልጅ ወደ ልጅ አንድ ዓይነት አይሆንም። ይህም ሂደት ወላጅነትን የሚያስፈራ እና የዕድሜ ልክ የመማር ሂደት እንዲሆን ያደርገዋል።የልጃችሁን ነፃነት ለመገንባት በጣም አስቸጋሪ ከሆኑት ነገሮች ዉስጥ አንዱ ጊዜ እና ልምምድ የሚወስድ መሆኑ ነው። አንድም ሆነ ሶስት ወይም አምስት ነገሮችን ለልጆ ማድረግ ብዙ ጊዜ ፈጣኑ እና ቀልጣፋው መንገድ መስሎ ሊታይ ይችላል፣ ነገር ግን ልጆች በራሳቸው ነገሮችን እንዴት ማከናወን እንደሚቻል እንዲማሩ ማድረግ በጊዜ ሂደት ጊዜያችሁን እና ጉልበታችሁን የሚቆጥብ ከመሆኑ በላይ፣ የበለጠ በራሳችዉ የሚተማመኑ እና እምነት የሚጣልባቸው ግለሰቦች እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል።