Write your awesome label here.

የቦጌ ፍልሚያ ፤ ችግር መፍታትን መማር

ትምህርት አምስት

እንኳን ደስ ያላችሁ በ"የቦጌ ፍልሚያ ኮርስ አምስት" ላይ በመድረሱ እንኳን ደስ አላችሁ! ውስብስብ በሆነችው ዓለማችን አስቸጋሪ ፈተናዎችን የመፍታት ችሎታ ሐቀኝነት፣ ጽናት እና ስሜታዊ ብልህነት ይጠይቃል። ራስን የማብቃት እና ችግርን የመቋቋም ጉዟችሁን ስትቀጥሉ፣ እርስዎ እና ልጅዎ ችግር በመፍታት ውስጥ ከአንድነት እና ከትብብርን የሚገኘውን ጥንካሬ እንድትመረምሩ ተጋብዛችኋል።

በዚህ ኮርስ ውስጥ የጋራ እርምጃ ተፅእኖን በሚያሳዩ በሀሳብ ቀስቃሽ ውይይቶች፣ በበይነተገናኝ እንቅስቃሴዎች እና በአነቃቂ ታሪኮች ውስጥ ይሳተፋሉ።

የምትማሯቸው ነገሮች፦

  • ጽናት የትሞላው ችግር ፈቺነትን መማር፡ በጫናው ውስጥ ችግር-መፍታት: አስቸጋሪ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ ውጤታማ ውሳኔዎችን ለማሳለፍ የሚያስችሉ ተግባራዊ ልምምዶችን ለማድረግ በመስተጋብራዊ ምናባዊ ሁኔታዎች እና በሚና-ትወናዎችን ውስጥ ይሳተፋሉ። ትግስት ሙናን ለማግኘት ከምታደርገው ቆራጥ ፍለጋ፣ ትኩረት በተሞላው የመረጃ መሰብሰብ እና መተንተን አማካኝነት ማንኛውንም ችግር በጽናት ለመፍታት የሚያስፈልገውን የአእምሮ ዝግጅት (ውቅረ-ልቦና) ይማራሉ።

  • ጥንካሬ በአንድ: ተግዳሮቶች በተሞላበት ዓለም ውስጥ አንድነታችን የተስፋ እና የመቋቋም ምንጭ ይሆናል። በዚህ ኮርስ ሁሉ ውስጥ በአንድነት መሰባሰባችን ድምፃችንን እንዴት እንደሚያጎላ እና እንዴት ለፍትህ እንድንሟገት ኃይል እንደሚሰጠን እንመረምራለን። ከአካባቢ ማህበረሰቦች እስከ ዓለም አቀፍ እንቅስቃሴዎች፣ አንድነት እንቅፋቶችን የማፍረስ እና ወደ ፍትሃዊ ማህበረሰብ የሚወስደውን መንገድ የመክፈት ኃይል አለው።



  • የስሜቶች ሐቀኝነት፦  ጾታ፣ ዕድሜ ወይም አካላዊ ቁመናቸው ምንም ይሁን ምን ሁሉም ሰዎች እውነተኛ ስሜታቸውን የመግለጽ ችሎታ አላቸው። ለምሳሌ ያህል ደስታን ውሰዱ - እሱ ጠንካራ ሰው ቢሆንም ስለ ሴት ልጁ ደህንነት የሚያሳየውን ጭንቀት ለመግለጽ አይፈራም። ምንም እንኳን ማህበረሰቡ ያንን ባይጠብቅበትም ስሜቱን በመግለጽ ሐቀኛ ለመሆን ያለው ፈቃደኝነት መተማመንን ለመገንባት እና ግንኙነቶችን ለማጠናከር ስሜትን በሐቀኝነት መግለጽ ያለውን አስፈላጊነት ያሳያል።

የጋራ ጉዞውን ይቀላቀሉ፦

ቤተሰብዎን የለውጥ አቀጣጣይ ለማድረግ ዝግጁ ነዎት? አሁን ይመዝገቡና ብርታትን የማጎልበት፣ ችግርን የመቋቋም እና ለማህበራዊ ለውጥ የሚደረገው የጋራ ጉዞ አካል ይሁኑ። 

አባል ይሁኑ። አሁን ይመዝገቡ።